Friday, August 08, 2008

የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ሶስተኛ ዙር አራተኛ አመት አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ

ሀረር, ሐምሌ 29 ቀን 2000 (ሀረር) - የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ሶስተኛ ዙር አራተኛ አመት አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሀረር ከተማ የክልሉ ምክር ቤት አዳራሽ ተጀመረ ።

በጉባኤዉ መክፈቻ የክልሉ ዋና ኦዲተርና የአፈ ጉባኤዉ ጽህፈት ቤት ያቀረቧቸዉን የ2000 የስራ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በማዳመጥ በሪፖርቶቹ ላይ ተወያየቷል ።

የክልሉ ዋና ኦዲተር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ነስረዲን አሊ ለጉባኤዉ ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት አመቱ የታየዉ የስራ አፈጻጸም አበረታች እንደነበረና በገቢና ወጪ ሂሳብ አሰራር ላይ ይህ ነዉ የሚባል የጎላ ጉድለት እንዳልታየ አስታዉቀዋል ።

የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አብዱል መሊክ በከር በበኩላቸዉ ባቀረቡት ሪፖርት በበጀት አመቱ የምክር ቤቱን አሰራር ለማጠናክር በተደረገዉ ጥረት አበረታች ተግባራት መከናወናቸዉን አስረድተዋል ።

ዴሞክራሲያዊ አሰራርን ተግባራዊ ለማድረግ በክልሉ በየደረጃዉ የሚገኙ ተቋማትን አቅም ለመገንባት ተደረገዉ ጥረት ፍሬያማ ዉጤት እያሰገኘ መሆኑን አስታዉቀዋል ።

በክልሉ እየተካሄደ ያለዉ አበረታች የልማት ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ መንቀሳቀስ እንደሚገባም አፈ ጉባኤዉ አስገንዝበዋል ።

ጉባኤዉ በተጨማሪ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙረድ አብዱል ሀዲና የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዜዳንት አቶ ኤልያስ ያህያ ባቀረቡት የ2000 የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በመወያየት ጉባኤዉ ሪፖርቱን በሙሉ ድምጽ ተቀብሎታል ።

ጉባኤዉ በነገዉ ዉሎዉ በክልሉ በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥና የሀረር ከተማን ልማት ለማፋጠን እንዲያስችል በተዘጋጀዉ ረቂቅ አዋጅና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ ለጉባኤዉ የወጣዉ መርሀግብር ያመለክታል ።

ሪፖ10፡25 ኤዲከ11፡00 - 11፡20 ጠሰድ = ጥ/አጥ

---END---

0 Comments:

Post a Comment

<< Home