Friday, August 08, 2008

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት 183 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በጀትና ዓዋጆችን አጸደቀ

ሐረር, ሐምሌ 30 ቀን 2000 (ሀረር) - የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አራተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ጉባዔ ለ2001 በጀት ዓመት የሚውል 183ነጥብ6 ሚሊዮን ብር በጀት፣ዓዋጆችና ሹመት በማጽደቅ ዛሬ ተጠናቀቀ።

ጉበዔው ለሁለት ቀናት ባካሄደው ጉባዔ በጀቱን ያጸደቀው የክልሉ ምጣኔ ሀብታዊና ማህበራዊ ችግሮች ለማቃለል በዘላቂነት ለማቃለል የሚያስችሉና የኅብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል የሚያበቁ ተግባራትን ለማከናወን መሆኑን በጉባዔው ላይ ከቀረበው ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል።

ከበጀቱ 116 ሚሊዮን ብር ለመደበኛ የተመደበ ሲሆን ቀሪው ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እንደሚውልም ተገልጿል።

ከበጀቱ የክልሉ መንግሥት 42 ሚሊዮን ብር ሲያሰባስብ ጉድለቱ ከፌዴረል መንግሥት ከሚገኝ ድጎማ እንደሚሟላ ተብራርቷል።

እንዲሁም የሐረር ከተማን ዕድገት ለማስጠበቅና የክልሉን የቤተሰብ ሕግ ዓዋጆችና የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሹመት አጽድቋል።

የሐረሪ ክልል ምክር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሐዲ ባደረጉት ንግግር በክልሉ ባለፉት ዓመታት በድህነት ላይ የተመዘገበውን ውጤት በያዝነው የበጀት ዓመትም ለመድገም በጀቱን ወጪ ቆጣቢ በሆነ አሰራርና የኅብረተሰቡን ጉልበት በመጠቀም ለማልማት አስፈጻሚ አካላት መረባረብ እንዳለባቸው አሳስበዋዋል።

ሪፖ 12፡10 ኤዲ ከ12፡10 -12፡30

---END---

0 Comments:

Post a Comment

<< Home